በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር የምርምር አገልግሎቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጿል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው የተቋሙን የምርምር ማዕከል ጨምሮ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴውን ተመልክቷል፡፡
የደሞዝ ማነስ፣ የትምህርት እና ጥቅማጥቅም አከፋፈል ወጥ አለመሆን፣ የውድድር ሂደቶች ሚዛናዊ አለመሆን፣ የጥናትና ምርምር በጀቶች ወደስራው ባለቤት አለመድረስ፣ የተማሪዎች የምግብ በጀት እጥረትና መኝታ ክፍል መጣበብ የሚሉት ከዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ጋር በነበረው ውይይት የተነሱ ነጥቦች ናቸው፡፡
የአሰራር ክፍተቶችንና የምርምር ውጤቶችን ኩረጃ ለመቀነስ ግልጽ የሆነ መመሪያ ማውጣት እንዳለበት እንዲሁም ከኑሮ ውድነት አንጻር የሀገራችን ኢኮኖሚ እስኪረጋጋ መንግስት የታክስ ስረዛ ቢያደረግ የሚሉት አስተያየቶች እና ሀሳቦችም ተነስተዋል፡፡